Tuesday, July 16, 2013

ሰላም ለሁላችሁ



ሰላም ለሁላችሁ፤- በእግዚአብሔር ቅናት እቀናላችኋለሁ እንደንጽህት ድንግል እናንተን ለክርስቶስ ላቀርብ ለአንድ ወንድ አጭቻችኋለሁና፡፡ 1ኛ ቆሮ 11 ያመኑ ሁሉ በመጨረሻው ሰርግ ወደ መንግስቱ ተሞሽረው እንዲገቡ በደም ቀለበት ታጭተዋል፡፡እግዚአብሔር በሰው ልጆች ላይ ያለው ዓላማ ሁሉ ለክርስቶስ እንዲሆኑ ነው፡፡ የሰውም መንፈሳዊ እድገት የሚሄደው ክርስቶስን ወደ መምሰል  ነው፡፡ ማንም ራሱን መስሎ እና የራሱ ሆኖ  እንዲኖር አልተፈጠረም፡፡ ራሱን እንዲመስል የተፈቀደለት የመጀመሪያው ሰው አፈር መስሎ ተበላሽቷልና፡፡እናንተ ወደ ማን እየተጓዛችሁ ነው? ምኞታችሁስ ማንን ለመምሰል ነው? የነፍሳችሁ ራስ/ባል/ ማነው? ሙሽርነታችሁስ ለማን ነው? የምትኖሩት እና የምትሞቱት ለማን ነው? የመኖራችሁ ዓላማ ምንድነው? ክርስቶስ ኢየሱስ አይደለምን? እርሱን እንደ ባዕድ እና ትርፍ መጠጊያ አድርጎ ማሰብ ከእናንተ ይራቅ! እርሱ ሁለተኛ ወይ ሦስተኛ ምርጫ የሆነላት ነፍስ ሚዛኗን ታስተካክል፡፡ ሁለትና ሦስት ባል ያገባች ሚስት አንዱን ብቻ ታግባ! በሏን ለብ አድርጋ የምትወድ ሚስት ባሏን በደንብ መውደድ እንደሚገባት ሁሉ ለታጨንለት ጌታ እውነተኛ ሙሽሮች ፍቅረኞች መሆን ይጠበቅብናል፡፡ እባካችሁ ለሌሎች ሼር አድርጉት

No comments:

Post a Comment