Wednesday, July 10, 2013

ሰላም ለሁላችሁ

ሰላም ለሁላችሁ፤- እግዚአብሔር ሰውን የሚረዳው ወይም/underesatand/ የሚያደርገው በምን መጠን እንደሆነ አስባችሁ ታውቃላችሁ? ሰው ለእግዚአብሔር ችግሩን ድካሙን ሲነግረው እርሱ የሚሰማው ከጀርባው ታሪኩ ተነስቶ ነው ከአስተዳደጉ፣ ከደረሰበት ማህበራዊ ተጽዕኖ፣ ከስነልቦና ችግሩ፣ ወንጌልን ካለመማሩ፣ የሰው እርዳታ ካለማግኘቱ፣ የተጎዳ ከመሆኑ ከእነዚህ ሁሉ ችግሮቹ ተነስቶ ይሰማዋል፡፡ ስለዚህም ጨክኖ አይፈርድበትም ይራራለታል እንጂ! አብዛኛው ሰው ብዙውን ጊዜ አንድን ሰው የሚዳኘው ስለሰውየው በሰማው ወይ አልፎ አልፎ ባየው ነገር ይሆንና ሳይራራ ይወስንበታል፡፡ መጥላት ካለበትም ከዚያ ቀን ጀምሮ ይጠላዋል ይሸሸዋል፡፡ ጌታ የተለየ ነው፡፡ ባለችግሩን ከችግሩ ሳያወጣ አይተወውም፡፡ ሰባራውን ጠጋኝ ነው፡፡ ተወዳጆች ሆይ እመኑኝ እግዚአብሔር ስለእግዚአብሔር እንደሰማነው አይደለም፡፡ እኛ እንኳ ሰው ስለእኛ እንደሚናገረው አይደለንም እኮ! አምላካችን ግን ምን ያህል መሃሪ፣ ምን ያህል ታጋሽ፣ ምን ያህል ረዳት፣ ምን ያህል ተሸካሚ ምን ያህል አስፈሪ፣ ምን ያህል ታላቅ፣ ምን ያህል ቅን ደግሞም ምን ያህል አስፈሪ እንደሆነ ማን ሊገምት ይችላል? እባካችሁ እግዚአብሔር ይቀፋችሁ አምላካችሁ ያኑራችሁ ጌታችሁ እንደገና ይስራችሁ፤

No comments:

Post a Comment