Tuesday, October 8, 2013

ሰላም ለሁላችሁ፤- ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከውጭ ከማባከን የመጣውን ልጅ ተቀብሎ ወደ ቤቱ እንዳስገባው እንደጠፋው ልጅ አባት ነው፡፡



ሰላም ለሁላችሁ፤- ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከውጭ ከማባከን የመጣውን ልጅ ተቀብሎ ወደ ቤቱ እንዳስገባው እንደጠፋው ልጅ አባት ነው፡፡ ያለምክንያት በምህረቱ ተቃባይ ነው፡፡ አንዳንዴ ቸርነቱ ለፍርድና ለሙግት ሰዎች አነጋጋሪ ነው፡፡ ምህረት ግን ከፍርድ በፊት እና በላይ ነው፡፡ ለዚህ ነው ከፍርዱ ቀን በፊት የፍቅሩና  የማዳኑ ቀን የቀደመው፡፡ ደግሞም ከቤቱ በግፍ ለሚወገዱ ሰዎች ከበር ቆሞ ከተስፋ መቁረጥና ወድቆ ከመቅረት የሚጠብቅ ነው፡፡ አይነስውሩ ሰው ጌታዬ አበራኝ ባለ ጊዜ ከምኩራብ ቢያስወጡትም ከበር ቆሞ ጠብቆታል፡፡ ልጆቹ ከእርሱ አይን ፊት ስላሉ በየትኛውም ሁኔታ በቂ ዋስትና አላቸው፡፡ ሉቃ 15;24  ዮሐ 9;35
እባካችሁ ለሌሎች ሼር አድርጉት visit www.ashenafigmariam.blogspot.com

No comments:

Post a Comment