Monday, September 2, 2013

ሰላም ለሁላችሁ፤- አንጥረኛው ወርቁን በእሳት የምታቃጥለው እስከ መቼ ነው ቢሉት ፊቴን እሳካይበት ነው አላቸው፡፡ ጌታችን እንደእሳት በሆነ መንገድና መከራ የሚያሳልፈን የራሱን መልክ ማለትም ቅድስናን፣ ትዕግስት፣ ለሰው መኖርን፣ ደግነትን፣ ጠንካራ ስብዕናን እንድንለብስ ነው



ሰላም ለሁላችሁ፤- አንጥረኛው ወርቁን በእሳት የምታቃጥለው እስከ መቼ ነው ቢሉት ፊቴን እሳካይበት ነው አላቸው፡፡  ጌታችን እንደእሳት በሆነ መንገድና መከራ የሚያሳልፈን የራሱን መልክ ማለትም ቅድስናን፣ ትዕግስት፣ ለሰው መኖርን፣ ደግነትን፣ ጠንካራ ስብዕናን እንድንለብስ ነው፡፡ በሚቆረቁር መንገድ ያስሮጠናል ግን ወፍራም ጫማ በእግራችን ላይ ያስርልናል፡፡ ሞልቃቃና ቅምጥል ገጽ እንዲኖረን አይሻም፡፡ ኩራት የሚናገሩ ከንፈሮች በእሳቱ እንዲቀደሱ ይሻል፡፡ኢሳ6;7  በእርሱ ላይ መመካታችን እንኳ ራስን ዝቅ በማድረግ ቸርነቱን በማግነን እንዲሆን ይሻል፡፡1ኛ ጴጥ 2;16 አብረውን የሚኖሩ በእኛ እንዲያርፉ አብረውን የሚውሉ ከልባችን በሚወጣው ሃሳብ እንዲሳቡ ትከሻችን የተወደደውን አምላክ መሸከሙን ዓለም እንዲመለከት በእሳት እንሰራለን፡፡ እግዚአብሔርን ገና አላወቅነውም በየቀኑ በትምህርት በይበልጥ ደግሞ በሕይወት ትግል ውስጥ እያየነው እንመጣለን ያን ጊዜ እግዚአብሔርን አይቼዋለሁ እና ሰውነቴ ድና ቀረች /ጵንኤል/ እንላለን::  www.ashenafigmariam.blogspot.com ይጎብኙት
እባካችሁ ለሌሎች ሼር ያድርጉት

No comments:

Post a Comment